![Jeba](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/09/16/1e9b6067f1c146e18ece0b09213b0883_464_464.jpg)
Jeba Lyrics
- Genre:Hip Hop & Rap
- Year of Release:2023
Lyrics
ከራስህ ጋር ለተግባባህው - ልብ ቅን ሰው
ሳቅ ጨዋታ ለምትወጂው - አንቺ ደግ ሰው
ለተማሪ ወዝ አደሩ - አንተ ትጉ ሰው
ባህር ማዶ ለምትኖረው - የሀገሬ ሰው
ጀባ መውደድሽን ጀባ ጀባ
ጀባ ፈገግታህን ጀባ ጀባ
ጀባ ጥበብሽን ጀባ ጀባ
ጀባ ስኬትህን ጀባ ጀባ
ሮጥ ሮጥ እንደአባወራ
ኑር ኑር እንደንጉስ አውራ
ሳቅ ሳቅ እንደው ለቀና ቀን
ወዝ ወዝ እንደው ለመጪው ቀን
ላይ ታች - ከጊዜ ጋር ጉዞ
ከመሻት ጋር ደምቆ
ከስኬት ጋር ልቆ
ሂድ ሂድ - በእርድና ቅኔ
በእውቀት ክዋኔ
በፍቅር ወኔ
እናጣፍጥ - ህይወት እናቅልል
እናግዝፍ - መውደድ እናብስል
እናንፅ - ትውልድ እናንቃ
እናውጣ ትስጦዖ እናብቃ
እጅ አትስጥ - ለክፉ ጠባይ
ለበላይ ነኝ ባይ
አትችልም ባይ
ጊዜ አትስጥ - ለመገፋፋት
ለመተቻቸት
ለመገማመት
ጆሮ አትስጥ - ሰው ገፊ ናቂ
ሀዘን አድማቂ
ጥላቻ አፍላቂ
እሺ አትበል - ፍርሃት አስፋፊ
ለሀገር አጥፊ
ወሬ ለፋፊ
ከራስህ ጋር ለተግባባህው - ልብ ቅን ሰው
ሳቅ ጨዋታ ለምትወጂው - አንቺ ደግ ሰው
ለተማሪ ወዝ አደሩ - አንተ ትጉ ሰው
ባህር ማዶ ለምትኖረው - የሀገሬ ሰው
ጀባ መውደድሽን ጀባ ጀባ
ጀባ ፈገግታህን ጀባ ጀባ
ጀባ ጥበብሽን ጀባ ጀባ
ጀባ ስኬትህን ጀባ ጀባ
እኛ የሳልነው - ልበ ብር
ውጣ ውረድ - ደፋ ቀና ማይገድበው በል
እኛ የፃፍነው - በችግር ሀሜት
ፍርሃት እጅ ማይሰጠው በል በል
እኛ ያለምንው - ለአዲስ ነገር ደፋር
የጥበብ እውቀት ሰው በል በል
እኛ የፈለግን እንደእርግብ የዋህ
እንደእባብ ብልህ ንቁ ሰው በል
ጥሩ መስራቱን ነው እንጅ ማን ምን አለ አይልም
መስጠቱን ነው እንጅ ቀኝ ሰቶ ግራ አያይም
ሰርቶ ማሳየት ነው እንጅ ሲፎክር አይውልም
ለክፉ ስራ እንጅ ለደግ ጆሮ-ዳባ አይልም
ከደስታ ያልራቀ - ያራቀቀ
ከመትጋት ያልቦዘነ - ያስታጠቀ
ከጤናው ያልጎደለ - የሰነቀ
ከህይወት ያልሸፈተ - የታረቀ
ትናንት ልጅ - ዛሬ ወጣት
ነገ ሽማግሌ አጠቁም ጣት
አሁን ናት የምትኖራት
ጊዜ ሳይቀድምህ ተቀበላት
ተቀበላት - ህልምህን - ተረከባት